ICT
በደጀን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ዓባይ በር የኅብረት ሥራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን ለዩንየኑ አጠቃላይ ሥራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግና ከባንኮች ጋር በሲስተም ለማስተሳሰር እንዲያስችለው የተሟላ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሶፍት ዌር የተሟላ ዲጅታል ሲስተም ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደጀን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ዓባይ በር የኅብረት ሥራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን ለዩንየኑ አጠቃላይ ሥራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግና ከባንኮች ጋር በሲስተም ለማስተሳሰር እንዲያስችለው የተሟላ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሶፍት ዌር የተሟላ ዲጅታል ሲስተም ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- በጨረታው መወዳደር የሚችሉ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ከፍለው ከዩኒየኑ ፋይናንስ ክፍል የጨረታ ዝርዝር ሠነዱን በመግዛት የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ የድርጅቱን ስም፣ ማኅተም እና በፖስታው በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጥሬ ገንዘብ ከሆነ በዩኒየኑ አካውንት በባንክ ገቢ አድርገው ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በዩኒየኑ ገቢ ደረሰኝ አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በፖስታ ውስጥ ታሽጎ መግባት አለበት፡፡ የባንከ አካውንት ንግድ ባንክ 1000019160924 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጥቅምት 30/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 9/2019 ዓ.ም ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 10/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ 4፡25 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን በከፊል መወዳደር አይችሉም፡፡
- ከጨረታው ጋር በተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ተገዥ የሚሆኑ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ሲሰተሙ ከሚሰራባቸው ዩኒየን ቢያንስ 2 ማሰረጃ ማምጣት አለባቸው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 51 30 12 34 /09 10 19 06 53 መደውል ይችላሉ፡፡
ዓባይ በር የኅብረት ሥራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-19 10:25
- Region: Amhara
- Publishing entity: Abay Bare Union Work Union Financial Savings and Loans Cooperatives Union private limited
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T12:55:16.000Z
- Source: Qelal Tenders