Other

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች የማዕድን ሀብት ጥናት ለማከናወን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ጥናቱን ማስደረግ ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች የማዕድን ሀብት ጥናት ለማከናወን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ጥናቱን ማስደረግ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN እንዲሁም የተጨማሪ እሌት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸው፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሁሉንም ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በሰም አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሠመራ ከተማ ከሚገኘው የአፋር ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. አሸናፊው ድርጅት፤ አሸናፊነቱ ታውቆ ውሉ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት በየወረዳዎች በመገኘት ጥናቱን ማከናወን ይጠበቅበታል።

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግልጽ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ሠመራ ከተማ በሚገኘው የአፋር ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ

  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  • ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0905 507 228 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Afar National Regional State Mineral Resource Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T10:29:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders