Textile, Garments and Uniforms
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ለቀዶ-ሕክምና ክፍሎች አገልግሎት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ብትን ጨርቅ (Reusable Medical Textiles) ግዥ እና በሲዳማ ክልል (አርቤጎና ወረዳ) እና በኦሮሚያ ክልል (ፈዲስ ወረዳ) ጤና ጣቢያዎች የእናቶች እና ሕፃናት ሕክምና ክፍሎች ዕድሳት ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተገለፁት ሁለት የጨረታ መደቦች ለመሳተፍ ፍላጎት ያለቸውን ድርጅቶች በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡-
ሀ. በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉት የቀዶ-ሕክምና ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ፡ ደረጃውን የጠበቀ ብትን ጨርቅ (REUSABLE MEDICAL TEXTILES FOR SURGICAL DRAPES AND GOWNS) --የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ፤
ለ. የግንባታ እና ሕንፃ ዕድሳት መደብ---- የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/
በነጠላ ለ(1) እና (2)
- በሲዳማ ክልል ውስጥ በሚገኘው የአርቤጎና ወረዳ ውስጥ የሚገኙና ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ጋር የሥራ ስምምነት ባላቸው የሙጮጮ፤ ሱምቡሩ እና ቡቹሳ ጤና ጣቢያዎች የእናቶች እና ሕፃናት ሕክምና ክፍሎች ዕድሳት፤
- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ በሚገኘው የፈዲስ ወረዳ ውስጥ የሚገኙና ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ጋር የሥራ ስምምነት ባላቸው የቦኮ፤ ፈቻቱ እና ነጋ ቦምባሳ ጤና ጣቢያዎችን የእናቶች እና ሕፃናት ሕክምና ክፍሎች ዕድሳት፤
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በቱመርካቶ ድረ ገፅ/2merkato.com/ https://tender.2merkato.com/ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር/10/ ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል የፋይናንስ ክፍል በመቅረብ በየመደቦቹ አንፃር የተገለፀውን የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ በመክፈል መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም በመደብ ለ ሥር ለተዘረዘሩት የግንባታ ሥራዎች፡ ለአርቤጎና ወረዳ ጤና-ጣቢያዎች ዕድሳት ይርጋለም ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል፡ እንዲሁም ለፈዲስ ወረዳ ጤና-ጣቢያዎች ዕድሳት ሐረር ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል በመሄድ የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ሁለቱንም የጨረታ መደቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ E-mail: [email protected]
ይርጋለም ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ስልክ ቁጥር +251-0462251915
ሐረር ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ስልክ ቁጥር +251-0256660011
Tender details
- Deadline: 2026-11-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በ2merkato.com ድረ-ገጽ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-11-21 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hamlin Fistula Ethiopia
- Buyer's registered address: Kolfe Keranyo Sub city woreda 09, House number 920 Betel Hospital Street behind Augusta Shirt Factory
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Qelal Tenders (Nov 12, 2026)
- Posted at: 2026-11-12T10:32:14.000Z
- Source: Qelal Tenders