Vehicle

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን /ኃ/የተወሰነ የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ይፈልጋል

Description

አፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን /ኃ/የተወሰነ፡፡ ከሰቆጣ ሳቃ 1834 ኩ/ል ከሰቆጣ ኒየርአቑ 1224.5 ኩ/ል እና ከሰቆጣ ፃታ 200 ኩ/ል በድምሩ 3258.5 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ይፈልጋል።

በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉ ትራንስፖርተሮች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1ኛ. በዘመኑ የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብርን የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ  የሚችሉ/የምትችል 

2ኛ. ከሚጓጓዘው የትራንስፖርት (የጭነት) አገልግሎትና የትራንስፖረት ፍቃድ) ጋር የተዛመደ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው የግብር ከፍይነት ምስክር ወረቀት (Tax payer identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የወዛደር የመጫኛና ማውረጃ በትራንስፖርተሩ የሚሸፈን ሆኖ መኪናው የመጫን አቅም ከ200 ኩ/ል እስከ 220 ኩ/ል በአንድ ጊዜ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።

3ኛ. ተጫራቾች የሚገዛውን የትራንስፖርት አገልግሎትና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብል ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ዋቢ ዩኒዬን ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን 

4ኛ. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ውል ከተፍጸመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (CPO) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋቢ ዩኒዬን ገቢ በማድረግ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ / ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።

6ኛ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም በስተጀርባ ከሚገኘው ዋቢ /ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ/ኃላፊነቱ የተወሰነ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ6ኛ ቀን /ስድስተኛው ቀን /3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7ኛ. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ ቆይቶ በ /በአስራአንደኛው/ ቀን ተጫራቾች |ህጋዊ ወኪል/ በተገኙበት ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል።

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን /ሶሰት ቀን /በፊት በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል።

9ኛ. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

10ኛ. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 1173/0941 821 789/0933 214 815 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ
ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-18
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ ቆይቶ በ6ኛ ቀን /ስድስተኛው ቀን/ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-18 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ ቆይቶ በ6ኛ ቀን /ስድስተኛው ቀን/ ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Wabi Farmers Cooperative Union
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 12, 2026)
  • Posted at: 2026-11-12T11:25:15.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders