Water Pipes and Fittings

በአማራ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት1. የቧንቧ እና መገጣጠሚያዎች
  • ሎት 2.የሲዊች ቦርድ ከነ ሙሉ አክሰሰሪውና ኤሌክትሮ መካኒካልእቃዎች
  • ሎት 3 የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች
  • ሎት 4.የክሎሪን ዱቄት
  • ሎት 5.የጽ/መሳሪያዎች ግዥ
  • ሎት 6 የውሃ ሞተር ፓምፕ ማስጠቅለል በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት እና ማስጠቅለል ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር / TIN / ያላቸው፤
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. የሚገዙ እቃዎችን እና የሚጠቀለለው የውሃ ሞተር ፓምፕ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /Specification / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት የዕቃውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻቸውን በመሙላት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ላይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ እና የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት ከጠኃቱ 3፡30 ላይ ተዘግቶ / ታሽጎ / ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የሚከፈት ሆኖ 16ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይምየበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፊበትን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈበትን ዕቃ /ንብረት / ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን ደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  10. ውድድሩ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ / ሎት/ ይሆናል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ከገቢ ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 1715 / 058 776 0015 /በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-28 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dejen City Water Supply and Sewerage Service
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T08:16:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders