Building Construction
በደ/ምዕ/ኢት/ህ ከ/መ/በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የመ/ደ/ፍ/ቤት በአማን ምድብ ችሎት የሚያገለግል የህንጻ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ህ ከ/መ/በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የመ/ደ/ፍ/ቤት በአማን ምድብ ችሎት የሚያገለግል የህንጻ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት በጨረታ ለመወዳደድ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዝቅተኛ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በደረጃ 5GC እና ከዚህ በላይ የሆነ ድርጅት።
- በዘርፉ የንግድ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያለው እና ኮፒውን አይይዞ ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- የቲን ነምበር/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ያለው/ላት።
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ ሲወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- የሳይት ምልከታ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታው ለ20 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ21ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን በሚ/አ/ከተ/አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዶክመት መግዛት ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመት ቴክኒካሉን አንድ ኦርጅናል እና 2 ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ ለብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ዶክመት ሙሉ ከሆነ ተጫራቾቹ ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታዎች ይከፈታሉ። ነገር ግን ዕለቱ ዝግ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይሆርባቸዋል።ያለበለዚያ ያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ከሰሩበት ተቋም ማቅረብ የሚችሉ እና ከአድቫስ ክፍያ በፊት 20% በመስራት አድቫስ ክፍያ ለመጠየቅ ፍቃደኛ የሆነ/ሆነች
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ ሚዛን ከተማ በርጌስ የሚ/አ/ከተ/አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 28 28 76 98 እና 09 17 15 17 12 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ ር የመጀ / ደረጃ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ለ20 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-04 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ለ20 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Mizan Aman City Administration Frist Level Court
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
- Posted at: 2026-11-14T08:51:07.000Z
- Source: Qelal Tenders