Pumps, Motors and Compressors

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE) በኤ.ዲ.ኢ.ዋይ (ADEY) ፕሮጀክት አማካይነት በሱሉልታ፣ ውሌ፣ ኤጀርሳ ላፎ፣ ዳንዲ፣ አምቦ፣ ሊቢን ጃዊ፣ ኢሉ ገን እና በኮ ቲቤ ወረዳዎች ለሚገኙ የወጣቶች ቡድኖች ለበጋ መስኖ ልማት የሚሆኑ የሞተር ፓምፖች ከውሃ መሳቢያ እና ማስወጫ ቱቦዎች ጋር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩጽ ዴቭሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative) ከMastercard Foundation በAti በኩል በሚደረግ አጋርነት Agricultural focused dignified employment for youth in Ethiopia (ADEY) የተሰኘውን ፕሮጀክት  እየተገበረ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ውጣቶችን በተለያዩ የሥራ ዕድሎች ላይ በማሳተፍ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማጠናከር ያሰሙ ሲሆን ከዋና ዋና ተወልዱም የወጣቶችን ቡድኖች በማቋቋምና በማጠናከር የተጣጡ የሰብል ምርቶችን በማምረት ላይ እንዲሰማሩ ማስቻል ነው።

በዚህ መሠረት HUNDEE በሱሉልታ፣ ውሌ፣ ኤጀርሳ ላፎ፣ ዳንዲ፣ አምቦ፣ ሊቢን ጃዊ፣ ኢሉ ገንና በኮ ቲቤ ወረዳዎች ለሚገኙ የተደራጁ የወጣቶች ቡድኖች በበጋ ወቅት የተመረጡ ሰብሎችን በመስኖ ለማልማት የሚያስችሉ የሞተር ፓምፖችን ከውሃ መሳቢያና መልሶ ማስወጫ ቱቦዎች ጋር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ፓምፖቹ ወጣቶች ግድቦችን በሠሩባቸው ወንዞች ውስጥ የሚገኘውን ውሃ በመሳብ ለመስኖ እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ናቸው።

የዕቃዎቹ ብዛት፣ ዝርዝር መግለጫ፣ ቴክኒካዊ መስፈርቶችና የማቅረቢያ ሁኔታዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጹ ይሆናሉ።

በዚህ ዓይነት የዕቃ አቅርቦት ሥራ ላይ ልምድ ያላቸው፣ የታደሰና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተገቢውን የግብር ክሊራንስና በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ሌሎች ሰነዶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን በ300.00 (ሦስት መቶ) ብር በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ።

ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% (ሦስት በመቶ) የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) HUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative ስም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በታሸገው የጨረታ ማቅረቢያ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማካተት አለባቸው።

የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማቅረብ የሚቻለው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይቻላል። ጨረታው በሰባተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ 011 558 3967 /011 558 2328/ 09 13 39 98 17

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 10:20
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hundee-Oromo Grassroots Development Initiative
  • Buyer's registered address: አዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ በቪላ ቨርዴ ሆቴል ገባ ብሎ
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T12:40:51.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders