Other

ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ የዛፎች ጂኦ-ታጊንግ (Tree Geotagging)፣ ምዝገባ፣ ክትትል እና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አገልግሎት ሰጪዎችን በይፋዊ የፍላጎት መግለጫ (EOI) አወዳድሮ መምረጥ ይፈልጋል

Description

ብቁ ድርጅቶች ፍላጎታችሁን አሳውቁን

ዛፍን ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ መለየት ፣ መመዝገብ ፣ ክትትል ማደረግና

በከባቢ አየር ላይ ያለውን ተደራሽ ተፅዕኖዎች ለመከታተል የቀረበ አገልግሎት።

የብቁ ድርጅቶች ፍላጎቶችን ማሳወቂያ የመጨረሻ ቀን: ዓርብ, ህዳር 18 2019

1. መግቢያ

ሳፋሪኮም ቴሌኮሚኒኬሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ ዘላቂነት ላላ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ሀብት ፣ ትክክለኛ ግብረ መልሶች ፣ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ እና ግልፅ ከሆኑ የኦካባቢ ንብረት ተፅእኖ ፈጣሪ አሰራሮችን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው፡፡ ይህ የፍላጎት ማሳወቂያ ጥያቄው (EOI) በGPS/GIS- ላይ በማተኮር በዛፍ ምዝገባና ካርታ ስራ፣ በከባቢ አየር ክትትል ፣ የደን/ስነ-ምህዳር ምዘና ፣ የካርበን ክምችት፣ የዲጂታል ዳታ ኢየያዝ እና የአካባቢ ተፅእኖ ክትትል ላይ ልምዱና ብቃቱ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪዎችን ለመለየት ያለመ ነው።

2. የአገልግሎቱ የተደራሽነት መሰን

ይህንን አገልግሎት ለመስራት የሚመረጠው አገልግሎት ሰጪ አካል ፤ የእያንዳንዱን ዛፍ የህይወት ዘመን በሙሉ ወይም በከፊል ፣ የተከላ አካባቢዎችን ፣ የዛፍ ዝርያ አይነት፣ የተተከለበት ቀን፣ የተስላ አጋር አካል ፣ አሁናዊ የዛፍ ቁመና  ፣መጠን ዕድሜ እና የፎቶግራፍ ማስረጃዎችን በተገቢው ሁኔታ በማደራጀት ማቅረብ ፤ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ የዛፍ ልየታ በማድረግ ፣ የመመዝገብ እና የመከታተል የማደርግ ብቃት እንዳላው ማሳየት አለበት :: ግልፅና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የካርበን መጠንን ማስላትና ክትትል በማደረግ የሌሎች የአካባቢ አስተዋጽኦዎችን መደገፍ ፤ የፍና የከባቢ አየሩን መሰረታዊ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ መመዝገብ ፣ ማዘመን፣ መተንተን፣ ማረጋገጥ እንዲሁም ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል የዲጂታል ካርታ ስራ፣ የዳታ አያያዝ፣ የማረጋገጫ እና የጥራት ማረጋገጫ ዘዴዎችን ማቅረብ ይጠበቃል ፡፡ ይህ ተጠባቂ የስራ ልምድ ማረጋገጫ ፣ ቀደም ሲል የነበሩ የክትትል ተሞክሮችን ፣ የመረጃ ጥራት ቁጥጥሮችን ፣ ዲጂታል ካርታ ስራዎችንና ሪፖርቶችን አብረው መቅረብ አለባቸው ፤ እንዲሁም ሳፋሪኮም የዛፍ እና የአካባቢ መረጃዎቹን የማግኘት እና የባለቤትነት መብቱን ማስቀጠል አለበት፡፡

3. የሚጠበቁ ውጤቶች

ዝርዝር የRFP መስፈርቶች መሰረት በማደርግ የሚጠበቁት ውጤቶች የሚከተሉትን ናቸው ፦

  • የዲጂታል የዛፍ መዝገብ እና GPS/GIS መረጃ ቋት የዛፍ/የተከላ አካባቢ መዛግብት፣ ልዩ መለያዎች፣
  • የጂኦግራፊያዊ አካባቢዎች እና የህይወት ዑደት መረጃዎችን የያዘ መሆን አለበት
  • ዲጂታል ካርታዎች፣ ዳሽቦርዶችና የክትትል ሪፖርቶች ፡ የተከላ ቦታዎችን፣ አሁናዊ የዛፍ ቁመና ፣ ህልውና ፣ ዕድገትን፣ ሁኔታንና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን የሚያሳይ መሆን አለበት ።
  • የከባቢ አየር ሁኔታ ተፅዕኖ እና የካርበን ግምገማ ሪፖርቶች ግምታዊ የካርበን ልቀት መጠን አወጋገድ ፣ ሌሎች ተጨማሪ ተፅዕኖዎችንና ድጋፍ ሰጪ ዘዴዎችን ያካተተ መሆን አለበት ።
  • የመስክ ላይ ስራዎች ማሳያዎች ፣ የፎቶግራፍ ማስረጃዋችና እና የመረጃ ጥራት ሪፖርቶች በጥራትና ባስተማማኝ ሁኔታ የተሰሩ የክትትልና ምዝገባ የሚያሳዩ መሆን አለባቸው ።
  • የተሟላ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠና ለጋራ የሚችል የመረጃ ቋት (Datate) ሳፋሪኮም ትክክለኛውንና ተገቢውን መረጃዎች የመጠቀምና ተደራሽ የሚያደርግ መሆን አለበት ፡፡

4. ፍላጎታቸው እንዲያሳዩ የሚጠበቁት ድርጅቶች መመዘኛ

ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩትን ማስገባት አለባቸው

  • ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ተያያዥነት ያለው የምስክር ወረቀትና ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት የተሰጡ ፍቃዶችና ምዝገባዎች።
  • የድርጅቱ መግለጫ /TIN/የየግብር ክፍያነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ፣ የVAT/ ፣ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ስም ምዝገባ (የሚመለከተው ከሆነ እና ተዛማጅ የምስክር ወረቀቶች።
  • የዛፍ ልየታ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ የ GIS ፣ የአካባቢ ተፈጥሯዊ ሀብት/ደን ክትትል፣ የስነ-ምህዳር መረጃ አሰባሰብና የካርበን ግምግማ ወይም ተመሳሳይ ስራዎች ላይ የተረጋገጠ ልምድ ያለው ።
  • በ GIS፣ በአካባቢ አስተዳደር፣ በደን ልማት፣ በካርበን ምዝገባ፣ በሥነ-ምህዳር ቁጥጥር ወይም በተዛማጅ
  • መስኮች አግባብነት ያላቸው የምስክር ወረቀቶች/ እውቅናዎች ያለው ።
  • የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን የሚያረጋግ ጡ የመረጃ ቋቶች (databases) የጂአይኤስ ሲስተሞች (GIS systems)፣ የሞባይል መተግበሪያዎች ፣ ዳሽቦርዶች ወይም የመስክ ስራ መረጃዎችን የማጠናቀር ልምዶች ያለው በ GIS/GPS በደን ልማት ስነ-ምህዳር፣ በአካባቢ ክትትል፣ በካርበን ምዝገባ፣ በመረጃ አሰባሰብና ትንተና ላይ ተፈላጊውን ልምድ ያካባቱ ሰራተኞች ዝርዝርና የትምህርት ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል።
  •  ከተለያዩ ተቋማት ጋር የነበሩ የደንበኛ አገልግሎቶችን ከነመገኛ አድራሻዎቻቸው ጋር የሚያቀርብ እንዲሁም ስራውን በተገቢው መልኩ ማገባደድ ስለመቻላቸው የሚያረጋግጡ የምስክር ወረቀቶች ወይም ሌሎች አግባብነት ላለው የልምድ ማረጋገጫዎችን የሚያቀርብ፡፡

5. ለጥሪው ማመልከቻ ስለማስገባት

  • ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች የፍላጎት መግለጫ (EOI) ምላሾቻቸውን በሶፍት ኮፒ ይህ ጥሪ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወደ bldssafarcom.et ማስገባት አለባቸው፡፡ የፍላጎት ማሳወቂያው ማቅረቢያው "EOI – Provision of Tree Geotagging, Registration, Monitoring and Environmental Impact Tracking Services" የሚለውን በግልፅ መጥቀስ አለበት፡፡

ቀጣይ ሂደትና ማስታወሻ

ነፍሪኮም የቀረቡትን የ (EOI) አመልካቾች ከተመለከተ በኋላ ገምግሞ ምዘናዎችን ሊሰጥ ይችላል ፤ በተጨማሪም ቀጣዩ የ(EOI) ሂደት አነስተኛውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ሊመርጥ ይችላል።

  • በዚህ የፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ላይ የንግድ ዋጋ መጠቀስ የለበት ፡፡
  • የፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ማቅረብ ሳፋሪኮም ውል ለመስጠት ወይም የግዥ ሂደቱን ለመቀጠል የገባውን ቃል ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም ።
  • የፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የሚወጡ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በአመልካቹ ይሸፈናሉ፡፡
  • ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ. የግማ, በማንኛውም ጊዜ የፍላጎት ማሳወቂያን (EOI) ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ማስታወሻ ለአመልካቾች

ሳፋሪኮም በዚህ የፍላጎት ማሳወቂያን (EOI) ዝርዝር ማብራሪያዎች ላይ የተቀሱ ጥቂት ወይንም ሁሉንም ሀሳቦች ሙሉ ወይም በከፊል የመምረጥ ወይም የመሰረዝ ሙሉ መብት አለው፡፡ እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች የመጨረሻ ስለሚሆኑ ከአመልካቾች ጋር ስለ ሁኔታው ከማሳወቅ ውጪ ምንም አይነት የደብዳቤ ልውውጥ ሳፋሪኮም አይደርግም፡፡ ሳፋሪኮም እና ስልጣን የተሰጣቸው ተወካዮቹ በዚህ ማመልከቻ የቀረቡትን ሰነዶች እና መረጃዎች ለማረጋገጥ ማንኛውንም ማጣራት ወይም ምርመራ የማድረግ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።


Tender details

  • Deadline: 2026-11-27
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-11-27 17:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Safaricom Ethiopia
  • Buyer TIN: 0073915295
  • Published on: Capital (Nov 15, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T12:48:08.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders