Accounting and Auditing, Accounting System Design
ዛጎል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር እ.ኤ.አ የ2026 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶችን በውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የሂሳብ መመርመር (ኦዲት) ስራ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዛጎል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እ.ኤ.አ የ2026 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶችን በውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የኦዲት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የፌዴራል ታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው።
3. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የግብር እዳ የሌለባቸው መሆኑን የሚገልፅ ወቅታዊ የታክስ ክሪላንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ።
5. የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ።
6. የስራ ልምድ ማረጋገጫ፡
7. ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚወስደውን ጊዜ በመግለፅ ሌሎች ለመወዳደሪያ ይጠቅሙናል የምትሏቸውን ሰነዶች በማቅረብ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የማመልከቻ ሁኔታ፡-
መስፈርቱን የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በታሸጉ ኢንቨሎፖች በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድታስገቡ እንጋብዛለን፡፡ አድራሻ፦ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጎርጎርዮስ አደባባይ ተሻግሮ ካስ ታወር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0930533560
ዛጎል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-11-27 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Zagol Oil Ethiopia P.L.C.
- Buyer's registered address: ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጎርጎርዮስ አደባባይ ተሻግሮ ካስ ታወር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802
- Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
- Posted at: 2026-11-17T10:43:03.000Z
- Source: Qelal Tenders