Building Construction

በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመደበኛ በ2019 በጀት ዓመት ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመደበኛ በ2019 በጀት ዓመት ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች

ሀ/ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃና በዘርፉ የታደሰ የንግድምዝገባና የስራ ፍቃድ

ለ/የቲን/Tin/ምዝገባ ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ሁሉ የወቅቱን ገቢያ ዋጋና በወቅቱ የምዝገባ ሰርተፍኬት

ሐ/ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

መ/ ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን ለግንባታዎችም መልካም አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችልና የግንባታውን ስራ በገባው ውል መሰረት የሚያስረክብ

ሠ/ የግንባታውን ወቅት በተዳጋጋሚ ማስታወቂያ ያልወጣበት

ረ/ ተጫራቾች ግንባታ የሚገነባበት ከኦዳ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሳይት ምልከታ ደብዳቤ ማቅረቡ አለባቸው ።

  • ተጫራቾች ከ “ሀ” እሰከ “ረ” የተጠቀሱትን የንግድ ፍቃድ የቫትና የግብር ከፋይነትን መለያ ቁጥር እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ኦርጅናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግደታ አለባቸው ፡፡
  • በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ የሰነድ ሽያጭ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር)ብቻ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 30 የስራ ቀናት በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/አስ/ር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/ አስተዳደር ብር 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም/በሙጫ/በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 የስራ ቀናት በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/አሰ/ር በመቅረብ ለዚሁ ስራ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይችላሉ ።
  • ግንባታዎች ፍቃዳቸው BC/GC/ ደረጃ 6 እና ከ6 በላይ /አሸዋ ኛ ደረጃ መሆን አለበት ።
  • በገቡበት ውል መሰረት ጊዜና ቀናትን ጠብቀው ሰረተው ማስረከብ የሚችል እና ከዚህ ቀደም የግንባታ ውል ያላቋረጡ መሆን አለባቸው ።
  • የመሃንዲስ አስተያየት ተቀብሎ ለመስራትና በሚሰጠው አስተያየት ተገቢውን ስራን ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ
  • የጨረታው ሳጥን በ30ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትበቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ሂደት አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
  • ከዋጋ ጥናቱ ከ5% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳደሪ ያለቅድመ ክፍያ ስራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን :: በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ / Arithmetic error /የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ስነ-ሰርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ። እስካሁን በዞን ደረጃ ግንባታ ስራላይ ተጫርተው አሸናፊ ሆነው ስራውን እየሰሩ ያሉት አፈፃፀማቸው ከ70 % በላይ
  • መሆናቸውን ከአሠሪ መ/ቤት የድጋፍ ደብደቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።
  • የመክፈቻው ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ 0917403723/0976802922/0917190831/0925163248 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ ።

የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-12-21
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-21 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን በቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kaffa Zone Tello Woreda Oda Primary Level Hospital
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T10:45:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders