Vehicle
አልማኮን የህንፃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን ሲሚንቶ ብረት እና የመሳሰሉት ከፋብሪካዎች ወደ ግንባታ ፕሮጀክቶች ለማጓጓዝ ለ2019 በጀት ዓመት ለአንድ ዓመት የሚያገለግል የትራንስፖርት አገልግሎት በመስኩ ከተሰማሩ ህጋዊ የትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
አልማኮን የህንፃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን ሲሚንቶ ብረት እና የመሳሰሉት ከፋብሪካዎች ወደ ግንባታ ፕሮጀክቶች ለማጓጓዝ ለ2019 በጀት ዓመት ለአንድ ዓመት የሚያገለግል የትራንስፖርት አገልግሎት በመስኩ ከተሰማሩ ህጋዊ የትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
1, ማንኛውም ድርጅት በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ቲን ነምበር፡ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተሸከርካሪወች የባለቤትነት መታወቂያ (ሊብሬ) ያላቸው።
2. በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጣቸውና በትራንስፖርት ባለስልጣኑ በማህበር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ያላቸው
3. ከመንግስት ተቋማት እና ከመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች ጋር አብሮ የሰራ እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል!
4, የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ አልማኮን ዋናው መስሪያ ቤት ቀበሌ 7 ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት በስራ ሰዓት በአካል በመገኘት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻዉ ጎን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ትክክለኛ የድርጅታችሁን አድራሻ በመፃፍ ሎጀስቲክስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 መመለስ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በ15ተኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታ መክፈቻው ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀረውም።
6. ቅዳሜ እስከ 6፡00 ድረስ የድርጅቱ የስራ ሰዓት ስለሆነ እንደ ግማሽ ቀን የሚቆጠር ይሆናል።
7. አስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
8. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት cpo ማስያዝ አለበት።
9. አሸናፊው ጨረታውን ማሸነፉ በተገለፀለት በ5/አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ብር 500,0000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ከታወቀ በባንክ በተመሰከረለት /cpo/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በገዥ ድርጅት ስም በማስያዝ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይሆን በራሱ ፈቃድ ጨረታውን እንደሰረዘ በመቁጠር ድርጅቱ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል።
10. ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚጓጓዙትን እቃዎች አይነት ከጨረታ ሰነዱ በዝርዝር የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት።
11. ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ምክንያት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0914340031 ደውለው መጠየቅ ወይም አልማኮን ዋናው መስሪያ ቤት ፔዳ መስመር ቀበሌ 07 ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት ፊትለፊት በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።
አልማኮን የህንፃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-12-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ተኛው ቀን 8፡00
- Bid opening: 2026-12-02 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ተኛው ቀን 8፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Almacon Building Construction Contractor P.L.C
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 18, 2026)
- Posted at: 2026-11-18T08:08:02.000Z
- Source: Qelal Tenders