Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል የሚውል

  • የጽህፈት እቃ፣
  • የጽዳት እቃ፣
  • የደንብ ልብስ፣
  • ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የመብራት እቃ፣
  • የቧንቧ እቃ
  • የተለያዩ ህትመቶች
  • ቋሚ የቢሮ እቃዎች
  • የመኪና ጎማና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ቋሚ እቃ ፈርኒቸር/
  • የግንባታ እቃ፣
  • መድሀኒቶች፣
  • የህክምና መሳሪያዎች እና መለዋወጫዋች፣
  • CCTV ካሜራ ገጠማ የእጁ ዋጋና ሙሉ ማቴሪያል እና የሰራተኛ የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ የሚሰራ የአጥር በር ስራና የግቢ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የላብራቶሪ ማሽኖችንና የኤክስሬይ ማሽኖችን ጥገናና ስርቪስ አመታዊ የእጅዋጋ እና የጭነት መኪና ኪራይ ማውረጃና መጫኛን ጨምሮ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጋብዛለን።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ

1. በሙያው ዘርፍ (በሚመለከተው በንግድ ስራ) የተሰማራና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው(ያላቸው)።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ያላቸው።

3. የግዥ መጠን 500,000.00 (አምስት መቶ ሽህ) ብርና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

5. የእቃውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል

6. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በናሙናው መሰረት ማቅረብ የሚችል ናሙናውን ከመ/ቤቱ ማገኘትይችላል።

7. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ በመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመልስ 200 ብር (ሁለት መቶ) ብር እየከፈሉ ከደቡብ ወሎ ዞን ከለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 41 መግዛት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢል ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው የባንክ ዋስትና ከሆነ ከ90ቀን በታች መሆን የለበትም።

10. የውል ማስከበሪያ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ 10% ማስያዝ የሚችል።

11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት አየር) ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በጥንቃቄ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም በማድረግ እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል የጨረታ ሳጥኑ 5፡15 ላይ ይታሸጋል።

12. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ላይ ይከፈታል ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

13. ጨረታው በሎት (በጥቅል ዋጋ)የሚወዳደር ይሆናል።

14. እቃው ገቢ የሚሆንበት ቦታ ደቡብ ወሎ ዞን አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ነው።

15. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

16. ተጫራቾች በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የስራ ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ አቀስታ ጠቅላላ ሆል ቢሮ ቁጥር 36 ድረስ በአካል በመገኘት (በቢሮ በስልክ ቁጥራችን 033 114 0366/ 09 27 40 37 36/ 09 15 54 10 90 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ

ማሳሰቢያ፡-

  • ሆ/ሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች አቤቱታ ካላቸው ውጤቱ በተገለፀ በተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ላወጣው ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት በጽሁፍ ማቅረብ አለበት።
  • መድኃኒት የህክምና መሳሪያ ጥገናና ሰርቪስ ሶፍትዌር የመኪና ጭነት ኪራይ ለአንድ አመት የሚቆይ ይሆናል።
  • ሁሉም ጨረታ በሎት/በድምር ዋጋ የሚወዳደር ይሆናል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-12-04
  • Bid closing time: 11:15
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛዉ ቀን 5፡15 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-04 11:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛዉ ቀን 5፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Akesta General Hospital
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 19, 2026)
  • Posted at: 2026-11-19T08:42:56.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders