Vehicles Purchase

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ የ2024/25 ምርት የሆኑትን አውቶሞቢል (Automobile Electrical car) ተሽከርካሪ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ የ2024/25 ምርት የሆኑትን አውቶሞቢል (Automobile Electrical car) ተሽከርካሪ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።

1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

2. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የተሸከርካሪ አስመጪነት ወይም አምራችነት ፍቃድ ያለው እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አሰፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

4. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋዉ 10% ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ እና ቴከኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።

8. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።

9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም።

10. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ዉል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።

11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

12. የጨረታ መክፈቻ ቀናት፤ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ :- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 8ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 11 91 83 29

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-12-04
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-04 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oro Assemble Group
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 19, 2026)
  • Posted at: 2026-11-19T10:12:51.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders