Equipment and Accessories

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት እቃና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢሃድ 014/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  • ሎት 1 የጋዜጣ መጠቅለያ ላስቲክ፣ የጋዜጣ ማሰሪያ ገመድ (ቃጫ) እና የህትመት ማጓጓዣ ዘመናዊ ጋሪ
  • ሎት 2. Mid-sized sound system
  • ሎት 3 በውል ለአንድ ዓመት የሚሰራ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 4 የዲኮር ጨርቅ መስቀያ ብረት (Adjustable Event Backdrop Frame)
  • ሎት 5 የScreen Accessories ግዥ

ስለሆነም፡ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር

  • ለሎት 1. ብር 50,000.00
  • ለሎት 2. ብር 100,000.00
  • ለሎት 3.ብር 100,000.00
  • ለሎት 4.ብር 50,000.00
  • ለሎት 5.ብር 100,000.00

በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው።

4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን 1ኛ ፎቅ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 156 9869

ኢ.ሜይል [email protected] 
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም መተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-12-05 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer's registered address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
  • Posted at: 2026-11-20T07:32:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders