Building Construction
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ስፖርት ፊልድ፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤት፣ የካናል ጥገና፣ የኮብል ጥገና እና የስላቭ ከልቨርት ጥገና ግንባታ ስራ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ስፖርት ፊልድ፤ የህዝብ መጸዳጃ ቤተ፤ የካናል ጥገና፣ የኮብል ጥገና
እና የስላቭ ከልቨርት ጥገና ግንባታ ስራ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ በጀት እና በፌደራል መንገድ ፈንድ በጀት በ05 ቀበሌ በ06 ቀበሌ እና በ01ቀበሌ ለሚሰራው ስፖርት ፊልድ ግንባታ ፤ በ04 ቀበሌ ለሚሰራው የህዝብ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ፤ በ02ቀበሌ ለሚሰራው 0.37 ኪሎ ሜትር የኮብል ጥገና ፤በ02 ቀበሌ ለሚሰራው 1.38 ኪሎ ሜትር የካናል ጥገና እና በረጵ ቀበሌ ለሚሰራው 9 የመሸጋገሪያ ድልድይ ጥገና ግንባታ ስራ ለመስራት በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ፡-
- በ05 ቀበሌ በ06 ቀበሌ እና በ01 ቀበሌ ለሚሰራው ስፖርት ፊልድ ግንባታ ሎት 01
- በ04 ቀበሌ ለሚሰራው የህዝብ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሎት 02
- በ02 ቀበሌ ለሚሰራው 0.37 ኪሎ ሜትር የኮብል ጥገና ሎት 03
- 1.38 ኪሎ ሜትር የካናል ጥገና ሎት 04
- በረጵ ቀበሌ ለሚሰራው 9 የመሸጋገሪያ ድልድይ ጥገና ግንባታ ስራ ሎት 05
1. ደረጃቸው ለአዲሱ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
1. ደረጃቸው ለጥገና GC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
02. ለስራው ህጋዊ አግባብነት ያለው ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና እድሳት ያደረጉ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TN ያላቸው የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
03. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘውትር በስራ ቀንና ሰዓት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 500 አምስት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
04. ተጫራቾች የጨረታውን የፋይናሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀያ ሁለተኛው ቀን /22/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በ05 ቀበሌ በ06 ቀበሌ እና በ01 ቀበሌ ለሚሰራው ስፖርት ፊልድ ግንባታ፤ በ04 ቀበሌ ለሚሰራው የህዝብ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ፤ በ02 ቀበሌ ለሚሰራው 0.37 ኪሎ ሜትር የኮብል ጥገና ፤ በ02 ቀበሌ ለሚሰራው 1.38 ኪሎ ሜትር የካናል ጥገና እና በረጵ ቀበሌ ለሚሰራው 9 የመሸጋገሪያ ድልድይ ጥገና ግንባታ ስራ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
05. ጨረታው በቀን ----30/03/2019- ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
06. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ማስከበሪያ ዋስትና በጀት በ05 ቀበሌ በ06 ቀበሌ እና በ01ቀበሌ ለሚሰራው ስፖርት ፊልድ ግንባታ ሎት 01 ብር 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
07. በ04 ቀበሌ ለሚሰራው የህዝብ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሎት ዐ2 ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር ማስያዝ አለባቸው
08. በ02 ቀበሌ ለሚሰራው 0.37 ኪሎ ሜትር የኮብል ጥገና ሎት 03 ብር /27,000 ሀያ ሰባት ሺህ ብር ብቻ ማስያዝ አለባቸው
09. 1.38 ኪሎ ሜትር የካናል ጥገና ሎት ዐ4 ብር 65,000 ስልሳ አምስት ሺህ ብር ማስያዝ አለባቸው
10. በረጵ ቀበሌ ለሚሰራው 9 የመሸጋገሪያ ድልድይ ጥገና ግንባታ ስራ ሎት 05 ብር 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ ትእዛዝ /CPO/፤ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ትእዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
11. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በፋይናንስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዛ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 25% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
14. ከ3 በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
15. የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ቼክ በግዥው ፈጻሚ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
16. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ ።
በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀያ ሁለተኛው ቀን /22/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-09 10:30
- Bid opening (note): 30/03/2019- ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kemise City Administration Urban and Infrastructure Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለአንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
- Posted at: 2026-11-20T08:17:07.000Z
- Source: Qelal Tenders