የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ሎት ሁለት የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የመኪና ጎማዎች፣ ሎት ሶስት የተለያዩ አምፒር ያላቸዉ የመኪና ባትሪዎች፣ ሎት አራት የተለያዩ የጋራዥ የወርክ ሾፕ መሳሪያዎች፣ ሎት አምስት የተለያዩ ለጋራዥ የሚሆኑ የህንፃ መሳሪያዎች ፣ሎት ስድስት የቶርኖ ስራዎች (machine shop) እና ሎት ሰባት የፖምፒስታ ስራዎች (injection pump repair) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለሎት አንድ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለሎት ሁለት ብር 400 (አራት መቶ ብር)፣ ለሎት ሶስት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለሎት አራት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር እና ለሎት አምስት ብር 400 (አራት መቶ ብር) ለሎት ስድስት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር እና ለሎት ሰባት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የጋራዥ አገልግሎት ማዕከል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያዩ በሰም በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የመኪና ጎማዎች ፣የተለያዩ አምፒር ያላቸዉ የመኪና ባትሪዎች፣ የተለያዩ የጋራዥ የወርክ ሾፕ መሳሪያዎች እና የተለያዩ ለጋራዥ የሚሆኑ የህንፃ መሳሪያዎች ናሙና (ሳምፕል) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለሎት ሁለት ብር 80,000(ሰማኒያ ሺ ብር) ለሎት ሶስት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር)፣ ለሎት አራት ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) እና ለሎት አምስት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ለሎት ስድስት ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር እና ለሎት ሰባት ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(Ethiopian industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መሳቤት)።

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ ፡- በስልክ ቁጥር 011 126-2045 ወይም 011 111-4561 በመደወል ወይም በአካል በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-15 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia's Industrial Inputs Development Enterprise
  • Buyer address: በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሐንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ|ቤት)።
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T11:59:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders