ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጎማን መልሶ ለመጠቀም በሚያከናውነው የምርት ሂደት ውስጥ በየጊዜው ከጎማ የሚወጣ ሽቦ እና ቁርጥራጭ ጎማ (Loop Wire, Fine Wire & Scrap Tire) በጨረታ አወዳድሮ የአንድ ዓመት ውል በመፈራረም ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2018
ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጎማን መልሶ ለመጠቀም በሚያከናውነው የምርት ሂደት ውስጥ በየጊዜው ከጎማ የሚወጣ ሽቦ እና ቁርጥራጭ ጎማ (Loop Wire, Fine Wire & Scrap Tire) በጨረታ አወዳድሮ የአንድ ዓመት ውል በመፈራረም ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራጮች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ አግባብነት ያለው እና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በተለምዶ ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና መ/ቤት GIW ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከታች የጨረታ መዝጊያ ተብሎ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከታች የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በግል ማህበሩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
6. የግል ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያ ቀን፡- ሚያዚያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡- ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት
ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
ዋና መ/ቤት GIW ህንፃ 2ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ +251 91 783 2984 /251 91 061 4251
Tender details
- Deadline: 2026-04-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-16 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ECOSCO RISING HONGOFA Plc
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T13:57:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.