የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05/18

ድርጅታችን የገዛውን ሸቀጣ ሸቀጥ፤ ስኳር፣ ሲሚንቶ እና የኢንዱስትሪ ጨዉ መነሻዉን ለሸቀጣ ሸቀጥ አ/አበባ ከሚገኘዉ የደርጅቱ መጋዘኖች፣ ለስኳር ከሁሉም የስኳር ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች እና አ/አበባ ከሚገኘው መጋዘኖቹ፣ ስሚንቶ ከሁሉም የስሜንቶ ፋብሪካዎች እና የኢንዱስትሪ ጨው ከሱማሌ ክልል አፍሬራ ዞን ሀርገሌ ዩኦ ጨው አቅራቢ ማህበራት እና ከአፋር ክልል አፍዴራ ጨው አቅራቢ ማህበራት ወደ ሚገኙት የድርጅቱ ቅ/ፎች ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ ለተለያዩ በክልል የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. በዘርፉ የታደሰ የንግደ ሥራ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ታክስ ክሊራንስ ሠረተፍኬት እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠረተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ /አትክልት ተራ/ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት ከሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሸቀጣ ሸቀጥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለስኳር ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) ለሲሚንቶ ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እና ለኢንዱስትሪ ጨው ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብቻ ከትራንስፖርት ታሪፍና ከብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ የተጠቀሱ ህጋዊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እና በአንድ ፖስታ በማሸግ ሚያዚያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባችዋል።

5. ጨረታው ሚያዚያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ ላይ የተገለፀውን ደንብና ግዴታ በሙሉ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-2250


Tender details

  • Deadline: 2026-04-14
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-04-14 10:10
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise
  • Buyer address: ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T14:00:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders