በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

.

የዕቃዎች እና የአገልግሎቶች ግዥ ዝርዝር በሎት

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

1

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ

40,000

2

የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) ግዥ

40,000

በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፦

  • ከላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በየዘርፉ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ፣ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  • አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡
  • ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ መ/ደ/ፍ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ ማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው የሚጸናበት ጊዜ ከ60 ቀናት በታች ሊሆን አይገባም።
  • ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ግዥ ክፍል ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። አሸናፊ ተጫራች ጥሪ ከተደረገለት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በስድስተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈረም ይኖርበታል።
  • አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን እያንዳንዱን ዕቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በትእዛዙና በቴክኒክ መግለጫው (Specification) መሠረት መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ርክክብ መፈጸም አለበት።
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 0911535203 / 0923705381 ይደውሉ።

በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Hawela Tula Sub City First Instance Court
  • Bid bond: 40,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:22:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders