Machinery and Equipment
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ የድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ የአቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ የእርሻ ትራክተር እና የእርሻ ማረሻ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ የድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተከራዩ ስም |
የሚሽጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የድጋሚ ድር ድር ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር ) |
የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ |
በድጋሚ የድርድር ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ሁኔታ |
|
1 |
አቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናዜሽን አገልግሎት መስጫ |
1. የእርሻ ትራክተር (በቁጥር 01) ብራንድ Massey Ferguson የስሪት ዘመን 2021 አቅም 112HP እና ሞዴል MF6711 2. የእርሻ ማረሻ (በቁጥር 01) ብራንድ OTMA የስሪት ዘመን 2019 ሞዴል O/QD70/E፤ |
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው፡፡ |
5,923,887.97 |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ነው፡፡ |
ሕዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00 |
በድጋሚ የድርድር ጨረታ |
በድጋሚ የድርድር ጨረታ መመሪያ
1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተደራዳሪ የታደሰ መታወቂያ ኮፒና የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ፤ የድርድር መነሻ ዋጋ 1/5ኛ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በማስያዝ እስከ ሕዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ አስከ 10፡00 ድረስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ወርክ አውት ዲቪዢን ማመልከቻ ይዞ መቅረብ ይቻላል።
2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ ፤ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ፤በኢት/ያ ልማት ባንክ በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
3. ንብረቱን በድርድር ጨረታ ተወዳድሮ ያሸነፈ ተደራዳሪ፡-
- የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ የታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
- ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ያስፈልጋል ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉምሩክ ቀረጥና ታስክ መክፈል ግዴታ አለበት።
4. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የድርድር ጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪ ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ ለተሸነፉ የድርድሩ ተጨራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
5. ንብረቱ በባንኩ ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት እቅድ ያለው ተደራዳሪ የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ- ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።
6. የድርድር ጨረታው አሸናፊ፤አሸናፊ ሆኖ አስፈላጊውን ሂደት ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባንኩ ንብረቱን ለማስተዳደር ያወጣውን ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ፤ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለበት።
7. የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዚን ወደ ሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ መትከያ፤ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል።
8. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 046-180-15-28/38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል።
9. የድርድር ጨረታ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ሕዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል።
10. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተደራዳሪ ተጨራች ከድርድር ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የድርድር ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-11-20 12:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer's registered address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T09:57:28.000Z
- Source: Qelal Tenders