በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/086/2018

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ/አ/ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።

7. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114 616 መጠቀም ይችላሉ።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-21 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration (ERA)
  • Buyer address: ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:28:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders