የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ2018 ዓ.ም ሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ2018 ዓ.ም ሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፦

1. ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣

2. ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር

3. ፕሪንተር

4. ካሜራ

5. ትራይፖድ

6. የካሜራ ሚሞሪ

7. ሌንስ

8. የካሜራ ባትሪ

9. የካሜራ ቦርሳ 

10. ገመድ አልባ ማይክ

11. ስፒድ ላይት

12. የስፒዲ ላይት ቻርጀር

በዚህም መሰረት በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶች ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀንና ዓ.ም ጀምሮ በቢሯችን ግዢ/ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝቶ በመውሰድ መወዳደር የሚቻል መሆኑን እየገለጽን፡-

1. በዘመኑ የመንግሥት ግብር የተከፈለበትና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው

2. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው

3. ከፌዴራልም ሆነ ከክልል መንግሥት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተሰጠ የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፣

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት መሆኑን መግለጽ ይገባቸዋል

5. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ተጨማሪ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

6. ተወዳዳሪዎች ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ በ specification መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲፒኦ፣ ባልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ስም አሠርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች ውል በሚገባው ስምምነት መሰረት አጠናቀው ማስረከብ እንዳለባቸውና በጊዜ ገደብ ውስጥ አጠናቀው ካላስረከቡ በውሉ መሰረት የሚጠየቁ መሆኑ፣

9. ጨረታው ይፋ ከሆነበት ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።

10. መሥሪያ ቤቱ የሚያጫርተውን ጨረታ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ብዛቱን እንደ ሁኔታው የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያና የማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ጨረታው ከመከፈቱ 3 ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።

12. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንሻልና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ከነ ኮፒው በ11ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡25 ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል።

13. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

14. ጨረታውን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0939 563 749 ደውሎ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመ/ኮ/ጉ/ቢሮ

/ሆሳዕና/


Tender details

  • Deadline: 2026-04-17
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡30
  • Bid opening: 2026-04-17 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopian's Regional State Government Communication Affairs Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:58:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders