የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ገቢና ወጪ ማድረጊያ ደረሰኝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ገቢና ወጪ ማድረጊያ ደረሰኝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት :-
1. አቅራቢው የተሰማራበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
2. የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚገልጽ ማስረጃ፤
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/
4. ከተሰማሩበት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ስለተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አቅራቢነት በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋጫ ማስረጃ፤
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ) ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ሕጋዊ ማህተም ያለው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በቂ ዋስትናና ለዋስትና ሊያበቁ የሚችሉ ማስያዣዎች 10% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመያዝ ደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርበው በመክፈል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ሠዓት የሚከፈት ሲሆን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በግልጽ ይከፈታል
12. የሚታተመውን የደረሰኝ ዓይነት /ናሙና/ ቢሮ መጥተው ማየት (የራሳቸውን ናሙና ማቅረብ ይችላሉ)
13. አሸናፊው ተጫራች የታተሙትን ደረሰኞች የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል
14. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-04-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-21 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Southwest Ethiopia People's Regional Government Cooperative Development Agency
- Bid bond: 12,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 06, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:20:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.