ጥቁር አባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጭ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተሸከርካሪ መለዋወጫ ጨረታ ማስታወቂያ

ጥቁር አባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጭ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መመሪያ መሠረት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን በሚገኙበት ኮምቦልቻ ጋራዥ እና አዳማ ቅ/ፍ ስቶር ዘወትር በስራ ሰአት በመሄድ የገዙትን ጨረታ ሰነድ በማሳየት ስፔር ፓርቱን በአካል ማየት ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሠነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ የጠቅላላ ድምሩ 2% ጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይቻላል።

3. ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናቶች ዘወትር በስራ ሰአት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ኮምቦልቻ ዋና መ/ቤት ገንዘብ ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛታ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና ኮምቦለቻ ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታው መዝጊያ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 በስራ ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ይከፈታል ነገር ግን 16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተቀመጠው ሰአት ላይ የሚከፈት እና የሚዘጋ ይሆናል።

7. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፋበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንት/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።በስምንት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም።

8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን በ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

9. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር ኮምቦለቻ 033 551 4219 አዳማ 022 112 6241 አዲስ አበባ 011 557 5115

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎ/ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-21 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tikur Abay Transport Private Limited Company
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T09:24:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders