በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቆርቆሮና ብረታ ብረት፣ የሲሚንቶ አቅርቦት እና የቢሮ እቃዎች ግዥ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መለያ ቁ/ግንአስ፦ 140/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-

  • ሎት 01 ቆርቆሮና ብረታ ብረት፤
  • ሎት 02 የሲሚንቶ አቅርቦት እና
  • ሎት 03 የቢሮ እቃዎች ግዥ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነበር) ሰርተፍኬት ያላቸውና ፣የሚሞሉት ዋጋ ከ200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው።

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢት. ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመከፍል መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሆኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና unconditional Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡45 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጃናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡ ውድድሩ በየሎት ምድብ ጥቅል ድምር ስለሆነ የሁሉም እቃ ዋጋዎች መሞላት አለበት።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 03333601249፤ 0913669714 ወይም 0913871466 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡45
  • Bid opening: 2026-04-22 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Lasta Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T09:36:31.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders