Printing and Publishing
የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ለፕሮግራም ማስተዋወቂያ እና ለአድቮኬሲ ስራዎች የሚውሉ የህትመት እና የማስታወቂያ (Printing, Promotional & Visibility) ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ NCO/0460/2026
የህትመት እና የማስታወቂያ
የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ለፕሮግራም ማስተዋወቂያ እና ለአድቮኬሲ ስራዎች የሚውሉ የህትመት እና የማስታወቂያ (Printing, Promotional & Visibility) ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ስለ ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (NCO)
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) በሚያዚያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. (License No. 6792) የተመዘገበ ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ በአእምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ (psychosocial support) እና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። NCO ከመንግስት ተቋማት፣ ከትምህርትና ጤና ዘርፎች፣ ከሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት (OPDs) ጋር በትብብር ይሰራል።
2. የሚፈለጉ ቁሳቁሶች ምድብ (Procurement Category / Lot)
- Lot F: Printing, Promotional & Visibility Materials (የህትመት እና የማስታወቂያ ቁሳቁሶች)
3. የጨረታው ተሳታፊዎች ማሟላት የሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ: በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ TIN እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የብራንድና ቴክኒክ መግለጫ (Brand & Specifications): ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ህትመቶችና የማስታወቂያ ቁሳቁሶች በሙሉ ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ (ለምሳሌ የፕሪንት ጥራት፣ የወረቀት ግራም/GSM፣ የጨርቅ አይነት/Material Type፣ የብራንዲንግ አሰራር) በግልጽ ማመልከት አለባቸው።
- የትራንስፖርትና ማጓጓዣ አገልግሎት ዲክላሬሽን (Transport Service Declaration): አቅራቢዎች ዕቃዎቹን እስከ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት (አዲስ አበባ) ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ወይም የማይሰጡ መሆኑን በፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸው ላይ በግልጽ መጥቀስ አለባቸው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Mandatory Price Quotation Format): ተጫራቾች በተሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Quantity Offered = 1) በመጠቀም የአንድ ዕቃ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ ተመን (Price of One Unit) ማቅረብ አለባቸው።
- የማስረከቢያ ጊዜና የጥራት ዋስትና: የአቅርቦት ጊዜ ሰሌዳ እና የህትመት ጥራት ማረጋገጫ ሳምፕል (Sample Proof) ማቅረብ አለባቸው።
4. የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ጊዜ ሰሌዳ
- የጨረታው ማስታወቂያ የሚወጣበት ቀን: ቅዳሜ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. / September 19, 2026
- የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ቅዳሜ ፣ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. / Saturday, October 03, 2026 ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ ማክሰኞ፣ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. /Tuesday , October 06, 2026 ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ።
አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛልን) በሁለት የተለያዩ ኢንቭሎፖች ታሽገው በተፈረሙ ፖስታዎች በማድረግ፣ በአጠቃላይ በሶስተኛ ጥቅል ፖስታ ውስጥ በማሸግ በናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 በአድራሻችን በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት
አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02
ስልክ፡ 0993252797 / 0945482424
ኢሜይል: [email protected] , [email protected]
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-06 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Natanim Charitable Organization (NCO)
- Buyer TIN: 0084298990
- Published on: 2merkato.com (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T09:49:59.000Z
- Buyer website: https://natanimethiopia.org/
- Source: 2merkato