Stationery

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ ቤቶች የተለያዩ የቋሚና አላቂ እቃዎችን

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2 ህትመት፤
  • ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 5 ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ፤
  • ሎት 6 የመኪና መለዋወጫዎች፤
  • ሎት 7 ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 8 የተሸከርካሪ ጥገና እና የጎሚስታ አገልግሎት ስራዎች በግልፅ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸውን ነጋደዎች በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

ስለዚህ በዘርፉ ላሉት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው።
  3. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ// ቡድን ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ በቁርጥ ለፅ/መሳሪያ 40000 (አርባ ሽህ ብር) ለኮምፒዩተር እና ተዛማጅ 30000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ለፅዳት ዕቃ 15000 (አስራ አምስት ሽህ ብር)፤ ለመኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 15000/አስራ አምስት ሽህ ብር እና ለሌሎቹ ለእያንዳንዳቸው ሎት ጨረታዎች 5000 (አምስት ሽህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  10.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ-28-/02/2019 ዓ.ም እስከ 7/03/2019 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የጨረታውን አይነት በመግለጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና የድርጅቱን ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና ፊርማ በመፈረም ማስታወቂያው ከወጣበት ከ-28-/02/2019 ዓም እስከ 8/03/2019 ዓ.ም የካላንደር መቁጠሪያ ቀናት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል።
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ-8/3/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/ስ/ሂ ክፍል በሮ ቁጥር 32 ይከፈታል።
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በጥቅል/ ሎት ወይም በነጠላ የማወዳደር መብት አለው።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 132 0801 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  17. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ ስራ የመስራት ግዴታ ይኖርባቸዋል።
  18. የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይቀየራል።
  19. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ከቫት በፊት ከነቫቱ እዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በሌለው መልኩ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ካልሆነ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል።
  20. ተጫራቾች ለሚገዙት ሰነዶች ከሰነዱ ጋር ከቀረበው የግዥ ሰነደ ጋር አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ማቀረብ ይኖርባቸዋል።
  21. ለማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከ20.000 ብር / ሃያ ሽህ ብር በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000 ብር አስር ሽህ ብር በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ከፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን ማወቅ አለባችሁ።

 የስራ ቦታ ዓለም ከተማ

አድራሻ:-  ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽቤት ስልክ ቁጥር 011 132 0801/ 395  

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-11-17 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shoa Zone Finance Department
  • Buyer's registered address: Deberberhan, Amhara
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T09:26:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders