Equipment and Accessories
በአማራ ብሄራዊ በክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ በክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- 1.ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ
- 2.ሎት 2 የቢሮ ቋሚ እቃ ፈርኒቸር/
- 3.ሎት 3 የእስፖርት ትጥቅ
- 4.ሎት 4 የእንስሳት መድሀኒት
- 5.ሎት 5 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል
- 6.ሎት 6 የመኪና ጎማ
- 7.ሎት 7 ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች
- 8. ሎት 8 የጽህፈት መሳሪያ
- 9. ሎት 9 የጽዳት እቃ
- 10. ሎት 10 የመኪና እቃ
- 11. ሎት 11 የደንብ ልብስ ጫማ
- 12. ሎት 12 ሱፍ መሰል ጣቃና ቲትረን 6000
- 13. ሎት 13 የተዘጋጁ ልብሶች
- 14. ሎት 14 ህትመት
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል
ስለዚህ
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው!
3 የተጨማሪ እሴት ታክስ /ሻት /ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4 ግዥ ከ500.000 በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6 የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 / አራት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢል ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 1% እና ከዚያ በላይ ከባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
9 ማንኛውም ተጫራች ግዢ በጥቅል /በሎት/ የሚፈጸም መሆኑን አውቆ የእያንዳንዱን ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርባቸዋል ሆኖም የተዘረዘሩትን እቃዎች በመሙላት ጠቅላላ ዋጋውን ያለመሙላት ስርዝ ድልዝ ማህተም ፊርማ ያለማድረግ ጭምር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቦረና ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ከጧቱ 4፡00 የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ወደም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ በተመሳሳይ ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 የሚከፈት መሆኑ ይታወቅ።
12 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. የንብረት ርከብክብ የሚፈጸመው ቦረና ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት እና ሴክተር መ/ቤቶች ነው።
14 በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ ከግዥ ጨረታ መመሪያው ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ወይም ስልክ 033 2405441 ወይም 0938429553 መደወል ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደ/ወሎ መስተዳደር ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-23 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Wollo Zone Borena Woreda F/E/D/B
- Bid bond: 1%
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:20:44.000Z
- Source: Qelal Tenders