የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦቲ ጫማ የወንዶች እና የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
1. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የስራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፤የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ ብር 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
5. የቴክኒካል ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ሰነድ 24/7/2018 ቀን እስከ 13/08/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተደረር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 14/08/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3.30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
8. ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-04-22
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-04-22 09:30
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Dawa Administration Police Commission
- Bid bond: 150,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:48:35.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.