የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመፀዳጃ ቤት ማስመጠጫ መኪና ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለፖሊስ ጣቢያ የሚሆን የመፀዳጃ ቤት ማስመጠጫ መኪና ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፤
|
ሎት 1 |
የሚገዙ እቃዎች የሎት ዝርዝር |
በሲፒኦ የሚገዙ የገንዘብ መጠን |
|
ሎት 1 |
የመፀዳጃ ቤት ማስመጠጫ መኪና |
2000 |
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፣
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተመሰከረለት
- የባንክ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት 60 ቀን ነው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች ሾላ ገበያ በሚገኘው በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ከስራ ቀናት ውጪና የክብረ በአል ቀናት ከዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሲሆን ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ካላንደር ዝግ ወይም ስራ የማይኖርበት ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 011 663 9002/ 011 667 6482
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-20 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Police Commission
- Buyer address: ኮልፌ ቀራዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምሪያ ከጦርኃይሎች በስተግራ ቀለበት መንገድ ሲወርዱ የቀድሞው ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ሳይደርሱ
- Bid bond: 2000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T09:39:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.