የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- ግ/ጨ/06/2018

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት በዞኑ ካፒታል በጀት የሚገነባውን ሌሎች የሚገዙ ዕቃዎች እና የሚሸጡ የሰው ሠራሽ ደን ዛፎች እስከ በጀት ማብቂያ ድረስ ማለትም ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ዋጋ ፀንቶ የሚቆይ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት

  • ሎት .1. የካፋ ዞን ፍትሕ መምሪያን የቢሮ ጥገና /ዕድሳት/ ለማስጠገን ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-9 የሆኑ በጥቃቅን እና አነስተኛ በግንባታ ዘርፍ የተደራጁ ማኅበራትን እርስ በርስ ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት፣
  • ሎት .2. የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያን የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-9 የሆኑ በጥቃቅን እና አነስተኛ በግንባታ ዘርፍ የተደራጁ ማኅበራትን እርስ በርስ ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት
  • ሎት 3. የካፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የጥበቃ ቤት፣ የመፀዳጃ ቤት ሴፕቲክ ታንክ በአንድነት እና የአጥር ግንባታ ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-5 ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት፣
  • ሎት .4. የካፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ባለአንድ ወለል ሥልጠና ማዕከል ግንባታ ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-4 ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት፣
  • ሎት .5. ለሴክተር መ/ቤቶች ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለመግዛት ለ3ኛ ጊዜ የወጣ እና
  • ሎት .6. የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 2018 ዓ/ም ቡኖ መጽሔት ለማሳተም ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  • የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ሰርቲፊኬት፣ የቲን/TIN/ ከገቢዎች ግብር ስለመክፈላቸው የተሰጠ ማስረጃ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  • ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  • ለሎት .1. ተጫራቾች ደረጃ GC/BC/ 9 የሆኑ ፣
  • ለሎት .2. ተጫራቾች ደረጃ GC/BC/ 9 የሆኑ ፣
  • ለሎት .3. ተጫራቾች ደረጃ GC/BC/ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ፣
  • ለሎት .4. ተጫራቾች ደረጃ GC/BC/4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
  • ሎት .5. ለሴክተር መ/ቤቶች ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለመግዛት ለ3ኛ ጊዜ የወጣ እና
  • ሎት .6. በካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 2018 ዓ/ም ቡኖ መጽሔት ለማሳተም
  • ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለሥልጣን መምሪያ ቀርቦ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ ለሎት .1.፣ ለሎት .2.፣ ለሎት .3. እና ለሎት .4. ሠላሳ/30/ ቀናት ሌላው ደግሞ ለሎት 5. እና ለሎት 6. አስራ አምስት /15/ ለተከታታይ ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO(Certified payment order) ጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ ለሎት.1. እና ለሎት.2. ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ፣ ለሎት 3 ብር 300,000.00 / ሦስት መቶ ሺህ ብር/፣ ለሎት -4- ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ ከቴክኒካል ኦሪጅናል ፖስታ ውስጥ በማስገባት ሌላው ደግሞ ለሎት -5- እና ለሎት.6. ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከቴክኒካል ኦሪጅናል ፖስታ ውስጥ በማስገባት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዢ ንብ/አስ/ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ለሎት.1.፣ ለሎት.2፣ ለሎት-3- እና ለሎት .4. ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንዳንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ በተለያዩ በሰም/በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ ቀናት ሌላው ደግሞ ለሎት .5. እና ለሎት .6. ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንዳንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ በተለያዩ በሰም /በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  • የጨረታው ሳጥን ሎት.5. እና ሎት.6. በ16ኛው ቀን እና ሎት.1. እና ሎት.2. ሎት.3. እና ሎት.4. በ31ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከሰዓት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል:: የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም:: 15 እና 30 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓላት ቀን ጨምሮ የሚቆጠር ነው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች አሠሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 331 1826 መጠየቅ ይቻላል

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ቦንጋ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-05-08 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kaffa Zone Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T12:52:24.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders