የሲዳማ/ብ/ከ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ፣ የቶታል ስቴሽንና ዲፈሬንሻል ጂ.ፒ.ኤስ ጥገና ግዥ፣ ፕሎተር ማሽን ጥገና ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ/ብ/ከ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎትየተገለጸውን ግዥ በዝርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ ግዥ
- ሎት 2. የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ
- ሎት 3. የቶታል ስቴሽንና ዲፈሬንሻል ጂ.ፒ.ኤስ ጥገና ግዥ
- ሎት 4 ፕሎተር ማሽን ጥገና ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፣
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 ሁለት መቶ ሺህ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፣
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 20.000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ብቻ በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ጨረታው የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እና የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11ተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 የሚከፈት ይሆናል፤
6, ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውንና ፈርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው።
7. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046221704 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:: የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ገብርዔል ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት ነው።
የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-04-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-20 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ተኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:19:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.