የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ ዕቃዎችን ወስደው የነበሩ እና በሊዝ ውሉ መሰረት የሊዝ ኪራይ ክፍያቸውን ባለመክፈላቸው ምክንያት የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ ዕቃዎችን በኪራይ ወስደው የነበሩ እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ ተከራዮች በሊዝ ውሉ መሰረት የሊዝ ከራይ ክፍያቸውን ባለመክፈላቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዮቹ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም

የሚሸጠው ንብረት

ብዛት

የድርድሩ መነሻ ዋጋ(ብር)

የሚጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

ኢሳኮር አግሮ ኬሚካል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

የግብርና ኬሚካል መርጫ ማምረቻ ማሽን

1

54,790,927.23

ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፤ ሞጆ ከተማ በድርጅቱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት /ቤት ሚያዝያ 20 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ

ሳሙኤል ተስፋዬ (ኢትዮ ሪሳይክሊንግ)

የእንቁላል መያዣ እና ለተለያዩ ምርቶች የሚያገለግሉ የወረቀት ምርቶች /Corrugated paper box/ የሚያመርት ማሽን እና ጄኔሬተር

1

4,491,726.84

ቢሾፍቱ ከተማ ባንኩ በቋሚነት የተረከበው የአቶ ሽመልስ ካሱ ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት /ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ

ቪኖቭል ጄኔራል ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማህበር

ለልብስ ስፌት የሚያገለግሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ቁሶች

58

3,995,931.64

ቢሾፍቱ ከተማ ባንኩ በቋሚነት የተረከበው የአቶ ሽመልስ ካሱ ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ

በኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪከት /ቤት ሚያዝያ 22 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 ላይ

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾቹ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾቹ ጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በመውሰድ የሚገዙትን የካፒታል ዕቃ እና የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ ከሆኑ መረጃዎች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተራ ቁጥር 1 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ፣ ለተራ ቁጥር 2 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እና ለተራ ቁጥር 3 እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው

3. ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በመወከል በጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

4. ካፒታል ዕቃውን መልሶ መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መሰፈርት ማሟላት እና ንብረቱን የሚከራይበትን ዋጋ፣ ስለ ቀሪው ኪራይ አከፋፈል ሁኔታ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሰገባት ይኖርበታል።

5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

6. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።

7. የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል::

8. በጥሬ ገንዘብ የሚገዛ የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨመሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎች እና የስም ማዛዋወሪያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል።

9. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰውን ማሽን አሸናፊ ተጫራች ማሽኑን ካለበት መጋዘን ነቅሎ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባላቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።

10. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-66-87 ላይ መደወል ይቻላል። ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-04-30 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T09:34:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders