የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የባህል አልባሳት እና የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት
- ሎት 1፡ የባህል አልባሳት እና
- ሎት 2 የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊያሟላ የሚችል መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ወቅታዊ ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ አና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፣ ከተራ ቁጥር 1-6 የተገለፁ የቅድመ-ብቃት መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከጨረታ ዉድድር ዉጪ ይሆናል።
7. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፣ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው፤ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከተማ አስተዳደሩ አካዉንት ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
9. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 (ለአስራ አንድ) ተከታታይ ቀናት ወይም እስከ መጨረሻ ጨረታ መዝጊያ ሰዓት/ 3፡30 ድረስ) በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም)፤ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ባልተገኙበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓል ቀን፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
11. የመንግስት መ/ቤቱ በዉል ወቅት በጨረታ ማስታወቂያ ወይም በጨረታ ሰነዱ በገለፀዉ የግዥ መጠን ላይ እስከ 20% ድረስ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-20 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:45:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.