Tyres, batteries and consumables

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ኦራል የእሳት አደጋ መኪና ጎማ በመስክ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ኦራል የእሳት አደጋ መኪና ጎማ በመስክ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

  1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ያላቸው
  3. ቲን ነምበር ያላቸው
  4. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ የጨረታ ዋስትና 50,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን እንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኃላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል።

ለበለጠ መረጃ 0467710211 ይደውሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ

አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኃላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኃላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Silte Zone Worabe City Administration FEDB
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Apr 10, 2026)
  • Posted at: 2026-04-11T07:28:34.000Z
← Back to all tenders