የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን መሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ከራይ ተከራይ በውሉ መሰረት የሊዝ ክራይ ክፍያውን ባለመክፈላቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ወይም የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ መልሶ ማከራየት ይፈልጋል።
|
የካፒታል እቃ ተከራይ ስም |
የሚሸጠው ንብረት |
ብዛት
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ(ብር) |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ደረጃ
|
ጨረታ የሚካሄደበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
አቶ አደፍርስ ክፍሌ
|
ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን
|
1set
|
29,733,095,25
|
አዳማ ከተማ፤ አባ ገዳ ክ/ ከ ደጋጋ ወረዳ በሚገኘው በተከራዩ መጋዘን ቅጥር ግቢውስጥ |
1ኛ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ ቤት ግንቦት 04 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20 (ሃያ በመቶ) የባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትረክት በመውሰድ የሚገዙትን የካፒታል ዕቃ እና የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- በጥሬ ገንዘብ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /ል /ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሽያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
- ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶች በመወከል በሸያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ባንኩ ለጥሬ ገንዘብ ተጫራች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ ካፒታል ዕቃውን መልሶ መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት መሟላት ይኖርበታል።
- አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከማዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒአ ተመላሸ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግሰት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል።
- የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የሰም ዝውውር ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን ካለበት መጋዘን ነቅሎ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብማነጋገር ወይም በሰልክ ቁጥር፡- 022-211-6687 ላይ መደወል ይቻላል። ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-12 10:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T08:02:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.