የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት የዶሎማይት ማምረቻ ማሽን እና አንድ ዊልሎደር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ የሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ከራይ ተከራይ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምከንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም |
የሚሸጠው ንብረት |
የሐራጅ መነሻዋጋ(ብር) |
የሚሸጠው ንብረትና ደረጃ የሚገኝበት ቦታ |
የሐራጅ ደረጃ |
ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
ኤክሶደስ ኬሚካል አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር |
የዶሎማይት ማምረቻ ማሸን እና አንድ ዊልሎደር |
64,093,679.68 |
ቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ክ/ከ ደደቻ ወረዳ በተከራዩ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
1ኛ |
በተከራዩ የማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡00-6፡00 |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንከ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሸያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
- ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶች በመወከል በሸያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሸ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል።
- የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛዋወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባላቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-6687 ላይ መደወል ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሃራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-05-07 12:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T08:38:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.