በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮምፒዩተር እና ጀኔሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።

  • ሎት 1:- ኮምፒዩተር..................የጨረታ ማስከበሪያ ብር 159600.00
  • ሎት 2፡- ጀኔሬተር....................የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80000.00

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ የሚያቀርብ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፡፡
  • በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል። .
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ሳምፕል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ሙሉ ሰነዱን ያላያያዘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
  • የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስያዣ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ 10% (ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ሊቀንስ ይችላል።
  • ተጫራቾች በመንግሥት ግዥ ዌብሳይት ላይ ድርጅታችሁ ተመዝግቦ መገኘት አለበት።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 276 8120 / 011 230 3241 / 011 230 3054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-25
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-25 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yekatit 23 General Secondary School
  • Buyer address: አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከአውቶቡስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 14, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T08:09:32.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders