የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ኦላይን የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000-70-96-80 882 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን አካውንት ላይ አስገብታችሁ ደረሰኙን ይዘዉ በመምጣት ሠነዱን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተገለፀው የዕቃዎች ምድብ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።

ሎት ቁጥር

የዕቃ ምድብ

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ሎት 1

የመኪና ኪራይ ግዥ

20,000

ሎት 2

ዲጂታል ሲቲ ማፕ ግዥ

50,000

ሎት 3

ሳውንድ ሲስተም

50,000

ሎት 4

ቨርቸዋል ቱር ግዥ

15,000

ሎት 5

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

50,000

ሎት 6

የህትመት ውጤቶች

20,000

4. ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን በየሎቱ በመከፋፈል /ቴክኒካል ኦሪጅናል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

5. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

6. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲ.ፒ.ኦ የጠቅላላ ዋጋው 10% ባማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በሚገኙበት ጨረታው በወጣው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አራዳ ክ/ከተማ፣ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ ቁ. 251-011-1-25-07-33

አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በወጣው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-23 10:15
  • Bid opening (note): ጨረታው በወጣው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T11:54:50.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders