Audio-visual, photography and graphic design

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ሐረር ከተማ ላይ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ሁለት ባለ 20 KVA ያገለገሉ PERKINS' እና LISTER ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ ሐረር ከተማ ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ጀነሬተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ-01/19

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል:: በዚሁ መሰረት ሐረር ከተማ ላይ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ሁለት ባለ 20 KVA ያገለገሉ PERKINS' እና LISTER ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ ሐረር ከተማ ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. ጀነሬተሮቹ በሚገኙበት፣ ሐረር ከተማ ቦቴ ናቲ ካፌ ህንፃ ስር በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ቅርንጫፍ እና ሻሽ ጋራጅ ፕላዛ ሆቴል አጠገብ በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ሃኪም ቅርንጫፍ በመገኘት ማየት ይችላሉ።

2. ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያዘዉ የገንዘብ መጠን ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ በዝርዝር ተቀምጧል።

3. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ ሐረር ከተማ ቦቴ ናቲ ካፌ ህንፃ ስር ከሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ቅርንጫፍ፣ ሐረር ከተማ ሻሽ ጋራጅ ፕላዛ ሆቴል አጠገብ ከሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ሃኪም ቅርንጫፍ እና የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት አዲስ አበባ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር መምሪያ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ጀነሬተር የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ጀነሬተሮቹን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሐረር ከተማ ቦቴ ናቲ ካፌ ህንፃ ስር በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታዉ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ባስገቡበት ሐረር ከተማ ቦቴ ናቲ ካፌ ህንፃ ስር በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ሐረር ቅርንጫፍ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን ጀነሬተር/ጀነሬተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል:: ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል።

9. በስልክ ቁጥር 0910 512 203 / 0955 022 308 / 0116 631 729 ደዉለዉ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-28 14:20
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan Bank S.C.
  • Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T13:43:41.000Z
← Back to all tenders