Audio-visual, photography and graphic design

ታምሪን ሞተርስ የተለያዩ አዳዲስ የሱዙኪ(SUZUKI) መኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል

Description

የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
ሽያጭ የጨረታ ሰነድ

ድርጅታችን ታምሪን ሞተርስ በኢትዮጵያ ውስጥ የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ወኪል አከፋፋይ የሆነው ኦሪጅናል የሆኑ የሱዙኪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ያለ ኩባኒያ ሲሆን፤ የተለያዩ አዳዲስ የሱዙኪ(SUZUKI) መኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው፦

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  • የ TIN ሰርተፍኬት
  • የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ
  • የተሞላ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ
  • የጨረታ ሰነዱን ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስያው ቀለበት መንገድ ላይ ከ DHL ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ ከሚገኘው የታምሪን ሞተርስ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ሳሪስ ኣደይ ኣበባ በሚገኘው ቅርንጫፍ መ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ጊዜ ይህ ጫረታ በጋዜጣ ታትመው ከወጣበት ቀን ጀምረው ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት።
  • የሰነዱ ዋጋ 1000 ብር (የማይመለስ)።
  • የጨረታ ዋስትና ማስያዣ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በ ሲፒኦ መልክ ማቅረብ አለባቸው።
  • ዋስትናው እስከ 6 ወር ድረስ የሚያገለግል መሆን አለበት።
  • ተጫራቾች ዕቃዎቹን ሁሉ ግዜ በስራ ሰኣት ሳሪስ አደይ አበባ ቅርንጫፍ በዋና የመለዋወጫ መጋዘን በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ።
    ኣሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ከቀረቡት የመለዋወጫ አይነቶች (items) ውስጥ ያሸነፉትን የመለዋወጫ አይነት ብዛት (quantity) የማንሳት ግዴታ ይኖርቦታል።
  • የዋጋ ማቅረቢያው በታሸገ ፖስታ (Sealed Bid) መቅረብ አለበት። የቀረበው ዋጋ የመጨረሻ ዋጋ መሆን አለበት።
  • የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ታምሪን ሞተርስ ዋና መሥሪያ ቤት ሁልጊዜ በስራ ሰዓት ለዚው ጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርቦታል።
  • ጨረታው በ 10ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  • መስፈርቱን ያሟሉ እና ከፍተኛ ዋጋ ያቀረቡ ተጫራቾች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
  • ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  • አሸናፊው ተጫራች ሙሉ ክፍያውን በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መፈጸም አለበት።
  • ኣሸናፊ ተጫራች ክፍያው ካልተፈጸመ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘውን ገንዘብ ለድርጁቱ ገቢ ይሆናል _
  • ሙሉ ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ አሸናፊው በ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ማንሳት አለበት።
  • የጭነት፣ የማጓጓዣ እና የማውረድ ወጪዎች በአሸናፊው ይሸፈናሉ።
  • ለሁሉም ተጫራቾች የሚሰጡ ማብራሪያዎች የጨረታ ሰነዱ አካል ይሆናሉ።
  • ለተጨማሪ መረጃ 09 33 64 13 71 / 09 30 10 28 52 ላይ መደወል ይችላሉ።

Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-18 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tamrin Motors
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T11:45:19.000Z
← Back to all tenders