አቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮምፒዩተሮች እና ጀኔረተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የአቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም ከታች የተዘረዘሩትን ቋሚ እቃዎችን በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል (ይፈልጋል)።

ተ.ቁ

የእቃው ዝርዝር

ሎት

የሚያሲዘው የብር መጠን በፐርሰንት

1

ጀኔረተር

ሎት 1

159,600.00

2

ኮምፒዩተሮች

ሎት 1

80,000.00

1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሰው እቃ በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

4.ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.go.et  ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚረጋገጥ ይሆናል።

6. ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ተደርጐበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት። ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የት/ቤቱ አድራሻ ከጳውሎስ ሆስፒታል ወደ መድሃኒያለም ት/ቤት በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ፋርማሲ ፊትለፊት ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 100 ሜ ገባ ብሎ በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው መሠረት ከ0.5 እስከ 2% ሲሆን ሎት ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ከጳውሎስ ሆስፒታል ወደ መድሃኒአለም ት/ቤት በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ፋርማሲ ፊትለፊት ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ በቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10 ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰው ዕቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ።

11. ሁሉም ተጫራቾችሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 005 ውስጥ ይሆናል።

13. ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተራ ቁጥር 11 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈጻሚ ይደረጋል።

14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

15 በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበት ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ስልጣን የተሰጠው አካል የተፈረመና የዋስትና ደብዳቤ ውል የጨረታ ማስከበሪያና ለውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።

16 አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።

17. የጨረታ አሸናፊነት ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብ እና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ

18. ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% cpo የውል ማስከበሪያ አሰርተው መምጣት አለባቸው።

19. አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኋላ እቃውን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት።

20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡ የቋሚ እቃዎች ተጫራቾች ትምህርት ቤቱ ባስቀመጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት ከሰነዱ ጋር የጄኔረተሩ በፎቶ ማስገባት አለባቸው። የኮምፒውተሩን ደግሞ በአካል ኮምፒውተሩን ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው። ሁሉም ቋሚ ዕቃዎች ከስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ዕቃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን። የሁሉም ቋሚ እቃዎች ስፔስፊኬሽን ፍላጐት መግለጫ/ በጨረታ ሰነዱ ክፍል ስድስት /6/ ውስጥ ማየት ይችላል።

ስልክ ቁጥር 011 273 2979 / 011 273 3515

አቢሲኒያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abyssinia General Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T12:31:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders