Generators and standby power
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የግርግዳ ስክሪን(WALL SCREEN INDOOR) እና ጀነሬተር 30KPA እና ከዛ በላይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት ለምክር ቤት አዳራሽ የግርግዳ ስክሪን(WAL SCREEN INDOOR) እና ጀነሬተር 30KPA እና ከዛ በላይ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት:-
1. የግድግዳ ስክሪን፣ ሎት ምድብ 01(አንድ)
2. ጀኔሬተር 30 KPA እና ከዛ በላይ ፤ሎት/ምድብ- 02(ሁለት)
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድረጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
1.በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች
2.በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደስ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፣
4.በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበ፤
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ለሎት 01 የጨረታ ማስከበርያ ብር፣ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት 02 ብር፣ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረለት ሲፒኦ (cpo) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰንድ ጋር ማቅረብ አለበት
7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማት/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካል ጉዳዮች በሚሸጥ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የሚገመገም ስለሆነ በጥንቃቄ መዘጋጀት ይጠበቅበታል።
9. የሚገዙት እቃዎች እስቶክ ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን መቅረብ አለበት (እስቶክ ውስጥ መኖሩ ግዴታ ነዉ)።
10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል።ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር: 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-17 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
- Posted at: 2026-08-06T07:31:02.000Z