Generators and standby power
በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ በ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ ውል በመያዝ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና ጀኔሬተር ግዥ በግልፅ ጨረታ አውጥቶ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ በ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ ውል በመያዝ
- ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና
- ሎት 2. ጀኔሬተር ግዥ በግልፅ ጨረታ አውጥቶ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 እና በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች እና የሚሰሩ ስራዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉን በተገኙበት በቡሬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- 10. የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ከሚቀጥሉት5 የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ) እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሶስት በመቶ ይቀነሳል፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞ ላውን በመምረጥ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈውን ጀኔሬተር አሸናፊ ተለይቶ ውል ከተያዘ በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በራሱ ወጪ እስከ ቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Bure First Level Hospital
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T11:35:47.000Z