በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት Desktop core i5 ኮምፒውተር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡-ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ 06/2018 ዓ.ም

በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 – Desktop core i5 /ኮምፒውተር

ስለዚህ በዚህ የሥራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች።

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 30,000 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፣
  7. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት ይሆናል።
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
  9. ናሙና መቅረብ አለበት።
  10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቸች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፣ ሕጋዊ ወኪል ለመሆናችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን።
  11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም ማድረግ አለበት። NAT| ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል፣ ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
  13. ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
  14. በጨረታው ላይ የዕቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
  15. በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል።
  16. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፣ ከተከፈተ በኃላ ናሙና የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
  17. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04

በስልክ ቁጥር -- 09 21 77 00 36 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡-በተፈለገበት ቀንና ቦታ በራሱ ትራንስፖት ማቅረብ የሚችል።

በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ /ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Administration Finance Office
  • Buyer address: አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T12:31:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders