በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የእንስሳት መድኃኒት እና ገረጋንቲ አቅርቦትና ሎደር ማሽን በሰዓት በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ባላቸው አካላቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2018
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ለእንስሳት ዘርፍ አገልግሎት እና በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የእንስሳት መድኃኒት
- ሎት2 ገረጋንቲ አቅርቦትና ሎደር ማሽን በሰዓት በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ባላቸው አካላቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ እና ስለመከፈሉ የገቢዎች ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ጨረታው የሚቆየው ከ05/08/2018ዓ.ም እስከ 26/08/2018 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በመሙላት ሶ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 8 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 26/08/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት ሶ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት የግዢ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁ/ር 8 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO 15000 /አስራ አምስት ሺህ/ ለእያንዳንዱ ሎት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፋው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈፅም በግዢ መመሪያ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውልመሰረት አሸናፊ የሆኑባቸው መድኃኒቶችና እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመድኃኒትና እቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 /ሶስት መቶ / በመክፈል ሰነድ መሰድ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ፡-046 883 0128
በማ/ ኢ/ ክ/ መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ቡኢ
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-05-04 11:00
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Sodo Woreda Finance Office
- Bid bond: 15,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-14T12:35:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.