የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ኢፕድ017/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ማጣርያ
- ሎት 2. በውል የሚሰራ የጽዳት አገልግሎት
- ሎት 3. በውል የሚሰራ የጥበቃ አገልግሎት
- ሎት 4. በውል የሚሰሩ የህትመት አገልግሎት ስራዎች በክልል ከተሞች (አዳማ፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ጂግጂጋ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ)
- ሎት 5. በዉል የሚሰራ የመጽሄት ህትመት አገልግሎት ስራ
ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ፋይናንስና ግዥ ዳት ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር
- ለሎት 1. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ለሎት 2. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ለሎት 3. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ለሎት 4. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት 5. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1ኛ ፎቅ በአቅርቦት መምሪያይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢ.ሜይል procurement@press.et
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፌት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-04-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-04-29 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 100,000.00 ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 14, 2026
- Posted at: 2026-04-14T13:26:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.