የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን/ Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1744/ሲ/ብ/ክ/መ/ኮ/ቢሮ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን/ Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፡-
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ እንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በተጨራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት 10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- የጨረታው መዝግያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል::
- ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያካትት መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካል ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ብሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 14, 2026
- Posted at: 2026-04-14T14:04:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.