በምስራቅ ጎ/አስ/ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የፈለገ ብርሀን ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የፋርማሲ ክፍል የአልሙኒየም (Apts) የግንባታ አገልግሎትና የእቃ አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎ/አስ/ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የፈለገ ብርሀን ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የፋርማሲ ክፍል የአልሙኒየም (Apts) የግንባታ አገልግሎትና የእቃ አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. በግንባታ ዘርፍ GC ስራዎች ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑ ተቋራጮች የግንባታ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
4. የግዥ መጠኑ ከብር 200.000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፈለገ ብርሀን ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ብድን ቢሮ ቁጥር 13 በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውንና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን ለማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታው ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና፤ በ2ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 የከፈታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ በአሸነፈበት የእቃውን (የአገልግሎቱን) ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 29 52 16 21/09 62 46 42 72 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የፈለገ ብርሃን ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታው ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና፤ በ2ኛው ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-05-04 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታው ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና፤ በ2ኛው ቀን በ4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: የፈለገ ብርሃን ጤና ጣቢያ
- Bid bond: 1.5%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-15T08:11:29.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.