የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ባሉብተ ሁኔታ  አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን

የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዝ የተገለጸ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 12/2018 ባሉብተ ሁኔታ  አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ/ቁ

ዘርፍ

የጨረታው አይነት

እቃዉ ያለበት ቦታ

1

የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (ፌሮ ብረት)

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

2

የፅዳት ዕቃዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

3

የፕላስቲክ ሸራ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

4

ኮስሞቲክስ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

5

ፈሳሽ ኬሚካል

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

6

ጫማዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

7

ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

8

ፓኪንግ ማሽን

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

9

የኮስሞቲክስ ዕቃዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ወርስ ዕቃ መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሱ መሆኑን እናሳውቃሰን፡-

1. በጨረታው ሸያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጰና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም ፡፡ በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ሌሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤

2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00_ 5፡0 ሰዓት የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የሰራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ኮስሞቲክስ ዕቃዎች (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና (ምድብ ዐ2) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ) ብር፤ እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተስው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁስ) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት

ግልጽ ጨረታ

እስከ 14/08/2018

15/08/2018 ዓ/ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል

2

ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት

ሐራጅ ጨረታ

እስከ 14/08/2018

15/08/208 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጠጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. የዕቃውን ናሙና (sample) ሳያይ የሚጫረት ተጫራች ቅ/ፅ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑ ይታወቅ።

11. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።

12. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 0332401510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
  • Bid opening: 2026-04-23 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Apr 16, 2026
  • Posted at: 2026-04-16T08:39:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders